(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.ጳጉሜ 4/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዎት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያና ጥምር ኃይሉ የሚያደርጉትን ልዩ ልዩ ድጋፎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
የኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በተወያዩበት ወቅት እንደገለፁት ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና ለጥምር ኃይሉ የአልባሳት፣ የደረቅ ምግብና የደም ልገሳ ለማድረግ ወስነዋል፡፡ ሠራተኞቹ ወደፊትም ለሠራዊቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ለመቀጠል ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች በ2013 በጀት ዓመት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን የአንድ ወር ደመወዝና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ http://localhost/feacc
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
የ ሀብት ምዝገባ እና ማሳወቅ:- https://feaccdars.gov.et/DARS_PL/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢ-ሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
ዩትዩብ፦https://www.youtube.com/channel/UCO_WiCAiDIkMMwqsZGK47nw
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡