የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ቢሾፍቱ ሥልጠና ማዕከል የመኝታ ክፍሎች እድሳት ዉስን ጨረታ ግዥ ሂደት በተካሄደ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ቢሸፍቱ የሥልጠና ማዕከል የመኝታ ክፍሎች እድሳት ለማከናወን በተካሄደ ውስን የጨረታ ግዥ ሂደት ላይ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት አካሂዷል።
በጥናቱ ግኝቶች ላይም ከኢንስቲትዩቱ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
ጥናቱ ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን በግልፅ ሳያወጣ ወደ ውስን ጨረታ መውሰዱን፣ የ መሀንዲስ ግምት ሳይሠራ በ45 ሚሊዮን ብር ይፈጸማል ተብሎ ህጋዊ አሠራርን ያልተከተለ ግምትን መነሻ በመውለድ ተጠይቆ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ምላሽ ከተሰጠ በኋላ ሌላ የመሀንዲስ ግምት መሠራቱን አመልክቷል።
ኮሚሽኑ በጥናቱ የተለዩትን ግኝቶች ግድፈቶች መሠረት አድርጎ፣ በውስን ጨረታ የተፈጸመው የኮንስትራክሽን ግዥ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአሠራር መመሪያን ያልተከተለ እና ግልፅነት የጎደለው በመሆኑ፣ ጨረታው ተሰርዞ የተፈጸሙ ክፍተቶች ተስተካክለው በፍትሃዊና ግልፅ በሆነ መንገድ እንደገና ጨረታ እንዲወጣ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል።
የኢንስቲትዩቱ አመራሮችም የቀረበውን የጥናት ምክረ ሀሳብ ተቀበለው ለመተግበር ተስማምተዋል።
ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕናን ይገነባል!
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

