+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ኮሚሽኑ “የሕግ አውጪው አካል አርአያነት፣ ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ፋይዳ” በሚል መሪ ቃል ለምክር ቤት አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 5/2018 ዓ.ም) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት አመራሮች የሕግ አውጪው አርዓያነት፣ ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ፋይዳ በሚል መሪ ቃል የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለሁለት ቀናት በኮሚሽኑ ተሰጥቷል።

በሥልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በተቋማት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር በየደረጃው ያሉ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም መንግስት ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማጠናከር የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታል ለማድረግ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ብለዋል።  ለዚህም መሶብ የአንድ አገልግሎት ማዕከል ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ተቋማት በተሰጣቸው ተልዕኮ ልክ እየሰሩ  በመሆኑ አሁን ላይ ስርዓታዊና ተቋማዊ ሙስና የለም ያሉት ም/አፈ-ጉባኤዋ፥ ከለውጡ በኋላ እየተሰሩ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና በጀት መጠናቀቃቸው ለዚህ ማሳያ ናቸው። ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች በሚፈጥሩት የግል ጥቅም ፍላጓት  አስተዳደራዊ ሙስና ይኖራል ብለዋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቴ አለነ በበኩላቸው ሙስናን ለመከላከል በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ መስራት ተተኪ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ገልፀወ፥ ህግ አውጭ አካልም በሥነምግባር አርዓያ በመሆን የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል ብለዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) በበኩላቸው የፀረ-ሙስና ትግሉ ቅንጅታዊ አሰራርን የሚፈልግ በመሆኑ የምክር ቤት አባላት ተቋማት በሙስና እና ብልሹ አሰራር ላይ  ትኩረት አድረገው እንዲሰሩ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሀገራችን ህዝብ የፀረ-ሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆን በርካታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፥ የህግ አውጭው አካል አራያነት፣ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ የላቀ ነው ብለዋል።

በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው ሙስናን ለመከላከል አገልግሎት አሰጣጥ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አወጋገድ እንዲሁም ተጠያቂነትን ማስፈን ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ተቋማት በትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ከእቅድ እስከ አፈጻጸም ድረስ እንዲሰሩ የምክር ቤቶች ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግ የገለጹት ደግሞ የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ ናቸው።

ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የህዝብ እሮሮ በሚበዛባቸው በአንዳንድ ተቋማት ላይ እየተከሰቱ ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ የምክር ቤት አባላት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አባላቱ ገልጸዋል።

ምክር ቤታዊ ተልዕኮ-ተኮር ሥልጠናው በዋናነት፣ የሕግ አውጪው አካል በሕግ ማውጣት ሂደት፣ በአስፈፃሚ አካል ቁጥጥር እና ክትትል፣ በምርጫ ክልል ውክልና ሥራዎች እንዲሁም በፓርላማ-መር ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች ከሙስና እና ብልሹ አሰራር ሥጋት እና ተጋላጭነት አስቀድሞ ለመከላከል አጋዥ የሆነ የግንዛቤ መፍጠሪያ መሆኑ ተመላክቷል።

የሥልጠና ተሳታፊዎቹ፣ በመድረኩ በርካታ ጉዳዮችን አንስተው የመከሩ ሲሆን፣ በሥልጠናው የተገኘውን ግንዛቤ ለቀጣይ ሥራዎች ግብዓት ለማድረግ መግባባት ተፈጥሯል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የፀረ-ሙስና ትግል፣ የመንግሥት ቁርጠኝነት የሚያመላክት መሆኑን የሥልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

በቀጣይነትም፣ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ሕዝባዊ መሠረቱን በማጠናከር፣ የትውልዱን ሥነምግባር በማነጽ እና ተቋማትን እየገነባን ለአገራዊ ብልጽግና ጉዞ የጎላ ሚና ከመወጣት አንጻር የምክር ቤቶች ሚና የላቀ በመሆኑ በቅንጅት የሚሰራ መሆኑ ተሰምሮበታል።

በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ፣ ሰብሳቢዎችና ም/ሰብሳቢዎችን ጨምሮ ከ300 በላይ የምክር ቤት አባላት ተሳትፈዋል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts