+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

የከተማ መሠረተ-ልማቶችን ውጤታማ ለማድረግ ሙስናን በጋራ ልንታገል ይገባል – ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 16/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን “የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፤ ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ሚና’’ በሚል መሪ ቃል ለከተማና መሠረተ-ልማት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ዘርፍ ተኮር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠና መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብረት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ሙስናን መታገል የመንግስት አቅጣጫ በመሆኑ በየደረጃው ያለ አመራር ትኩረት በመስጠት መስራት አለበት ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም ይህን መሰል ሥልጠና በየጊዜው በመስጠት የአመለካከት ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም የከተማና መሠረተ-ልማት ዘርፍ በባህሪው ለብልሹ አሠራር ተጋላጭ በመሆኑ አመራሩ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተጠንቅቆ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በተለይ የከተማ ልማትና መሠረተ-ልማቶችን ውጤታማ ለማድረግ ሙስናን በጋራ ልንታገል ይገባል ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ካስቀመጧቸው አምስቱ የመቀነስ ግቦች አንዱ ሙስናን መቀነስ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

በየደረጃው ያሉ አመራሮች ለሙስና እና ብልሹ አሰራር እንዳይጋለጡ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ መጠንቀቅ አለባቸው ብለዋል፡፡

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም የሙስና ዋነኛው መንስኤ የአመለካከት ዝቅጠትና የማህበራዊ እሴቶች መሸርሸር መሆኑን ገልፀው፤ ሁሉም አካላት በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ዘርፍ ተኮር ሥልጠናው የኮሚሽኑ የፀረ-ሙስና ትስስር አባል በሆኑት በዶ/ር ዮሃንስ ጴጥሮስ እና ዶ/ር ዩሱፍ ኢብራሂም የተሰጠ ሲሆን፤ ስልጠናው በዋናነት ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከል እና ማስተዳደር በሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በስልጠና መድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች፣ ሀሳቦችና አስተያየቶችን አንስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በስልጠናው የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የክልልና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ-ልማት ቢሮ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts