+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ኮሚሽኑ ከሰላም ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሄደ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 25/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ‘‘የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፤ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ!’’ በሚል መሪ ቃል ከሰላም ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ-ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሂዷል።

ስልጠናዊ ውይይቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ ዋና ዋና የሙስና ሥጋት እና ተጋላጭነት መገለጫ የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እና ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት ማስተዳደር ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ትኩረት ያደረገ ነው።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ ኢድሪስ አመራሮች ውሳኔዎችን ሲወስኑ ምን ያህል የህዝብን ጥቅም አስቀድመናል የሚለውን በማሰብ ከጥቅም ግጭት በጸዳ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የመንግስት አስተዳደር ባለቤት ህዝብ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ህዝብ የሰጠንን ሀብት ከሙስናና ብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ እንድናስተዳድር ኃላፊነት አለብን ብለዋል።

ሚኒስትሩ በንግግራቸው አስተሳሰብና አመለካከት ላይ ካልተሰራ ሙስናን በሀብት ማስመለስና በህግ ማስከበር ብቻ መከላከል ያስቸግራል ሲሉ ተናግረዋል።

ውጤት የሚመጣው ነጻ የሆነ የአሰራር ስርዓት ሲገነባ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ስራዎች መርህ ተኮር መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ እንዲህ አይነት ስልጠናዊ ውይይቶች የሞራል ልዕልና እንዲኖረንና እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደረጉ ናቸው ብለዋል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽን ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ አመራሩ ቁርጠኛ መሆን እንዳለበት ጠቅሰው፣ መንግስት የህዝብን አደራ ወስዶ እየሰራ በመሆኑ አመራሩ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት የህዝብን ጥቅም በማስቀደም መስራት እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ስነ ዜጋ ላይና የህዝብ ንቅናቄ ስራዎች ላይ የሚሰራ በመሆኑ ከኮሚሽኑ ጋር የጋራ ተልዕኮ አለው ያሉት ም/ኮሚሽነሩ፣ በዚህም የትውልድ ሥነምግባር ግንባታን በተቀናጀ መልኩ መስራት አለብን ብለዋል።

በውይይቱ መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና ሙስናን የሚጸየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ያሉት ደግሞ የሚኒስቴሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሳ መንግስቱ ናቸው።

በስልጠናዊ ውይይቱ ስለ ጥቅም ግጭትና ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሰፊ ግንዛቤ እንዳገኙ ተሳታፊዎች የገለጹ ሲሆን፣ በመጨረሻም ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችንና ሀሳቦችን አንስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ትውለሰድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts