+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ከ15 ዓመታት በላይ የተጓተተው የመገጭ ግድብ ፕሮጀክት….

ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ዞን እየተገነባ የሚገኘው የመገጭ ግድብ ፕሮጀክት በምዕራብ ደምቢያ እና ምሥራቅ ደምቢያ ወረዳዎች እስከ 17,000 ሔክታር የመስኖ እርሻ ማልማትና ለጎንደርና ዙሪያ ከተሞች ንፁህ የመጠጥ ውኃ እንዲያሚያቀርብ ዓላማ ሰንቆ የተጀመረ ፕሮጀክት ነው፡፡
ነገር ግን ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች በታቀደለት ጊዜና በጀት መሠረት ሳይከናወን ለበርካታ አመታት ቆይቷል።
የፕሮጀክቱን መዘግየት በሚመለከት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት የአሰራር ስርዓት ጥናት አካሂዶ ከተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዶ ነበር፡፡ በጥናቱ እንደተመላከተው ፕሮጀክቱ ዘገይቶ የመቆየቱ ምክንያት የበጀት እጥረት መኖር፣ የተቋራጭ ድክመት፣ የግንባታ ጥራት ጉድለት፣ የካሳ ከፍያ ችግርና የአማካሪ አቅም ድክመት ይጠቀሳሉ።
ከሰሞኑ በቦታው ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ የመገጭ ፕሮጀክት በመጪዎቹ ስምንት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት ካስተላለፉት የተለየ ውሳኔ በኋላ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽንን ከስራው በማስወጣት አዲስ ኮንትራክተር ገብቶ እንዲሰራ መደረጉን ተናግረዋል። “ከውጭ አማካሪዎች አምጥተን ጥናት አድርገን፤ ሲሠራ የነበረበት ቴክኒካል ችግር ከሥር መሠረቱ መፍትሔ እንዲያገኝ ካደረግን በኋላ ፕሮጀክቱ አሁን በጤናማ የፕሮጀክት አመራር ሥርዓት እየሔደ ያለ ፕሮጀክት ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦታው ጉብኝት ካደረጉ በኋላ የወንዝ ቅልበሳ ሥራ ተጠናቆ የቀሩት ተግባራት በጊዜ ሰሌዳ እየተከናወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በአካባቢውን የግብርና ምርታማነት ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን እናድርግ!

ለበለጠ መረጃ ዊብ ሳይታችንን ይጎብኙ
👇👇👇
https://www.feacc.gov.et

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

Related Posts