+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

የኩባንያው የቀድሞ ሊቀመንበር በሙስና ወንጀል የእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ

የቻይናው የንብረት ግዙፍ ኩባንያ ኤቨርግራንዴ የቀድሞ ሊቀመንበር ሹ ጂያይን በከባድ የገንዘብ ማጭበርበርና የሙስና ወንጀሎች ጥፋተኛ በመሆናቸው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው።

የሼንዘን መካከለኛ የሕዝብ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ፣ የሹ ጂያይን የግል ንብረታቸው በሙሉ እንዲወረስ እና የፖለቲካ መብታቸውን በእድሜ ልክ እንዲነጠቅ፤ ከወንጀል የተገኙ ሕገወጥ ገቢዎች እንዲመለሱ እና ጉድለት ካለ እንዲሟላ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ እንዳረጋገጠው፣ ሹ ጂያይንና እሳቸው የሚመሩዋቸው ኩባንያዎች የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማጭበርበር፣ የንብረት ዋጋን በማጋነን፣ ዕዳዎችን በመደበቅ እና የገንዘብ ተቋማትን ለመቆጣጠር ጉቦ በመስጠት ተጠቃሚ ሆነዋል።

እነዚህ ድርጊቶች የኩባንያውን የፋይናንስ ችግር ከማባባስ በተጨማሪ ባለሀብቶችን፣ ተቋማትንና ሕዝብን ከፍተኛ ኪሳራ እንዲያጋጥማቸው አድርጓል ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ ኤቨርግራንዴ ግሩፕና የሪል እስቴት ክፍሉ በድምሩ 15.82 ቢሊዮን ዩዋን ቅጣት ተጥሎባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች 56 ተከሳሾች ከ1 ዓመት ከ10 ወር እስከ 18 ዓመት የሚደርስ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

የኤቨርግራንዴ ጉዳይ በአንድ ትልቅ ኩባንያ ውስጥ ከፍተኛ ሙስና፣ ሥልጣንን አላግባብ መጠቀምና የፋይናንስ ማጭበርበር በአንድ ላይ ሲጣመሩ ምን ያህል ከባድ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚያሳይ ሆኗል ተብሏል።

ቻይና ዴይሊ እንደዘገበው፣ የሹ ጂያይን ጉዳይ ከፍተኛ ሥልጣንና ሀብት ከሕግ በላይ እንዳልሆነ የሚያስጠነቅቅ ጠንካራ መልዕክት እንደሆነ ተመላክቷል።

Related Posts