+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ሥነምግባር ያለው እና በባህሉ የሚኮራ ትውልድ ማፍራት ከሁሉም ይጠበቃል –  ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከባህልና ስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሂዷል።

ስልጠናዊ ውይይቱ የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፤ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ! በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን፤ በሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭትን መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

በስልጠናው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ዘርፉ በሀገረ-መንግስት ግንባታ ውስጥ ትልዕቅ ተልዕኮ የተሰጠው ዘርፍ ነው። ለዚህ ደግሞ ሥነምግባር ያለው እና በባህሉ የሚኮራ ትውልድ ማፍራት አንዱ በመሆኑ ስራውን መስራት ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።

በዘርፋችን ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ አሰራሮችን በመለየት እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ ይህ ስልጠና ከፍተኛ አመራሮች በዕለት ተዕለት በሚሰሯቸው ስራዎች ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲሰሩ ግንዛቤ ይፈጥራል ብለዋል።

አክለውም  ሙስናን ከመፈጸሙ በፊት ለመከላከል ግንዛቤ መፍጠር በሀገራችን የተጀመረውን የፀረ-ሙስና ትግል ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው አመራሮች ውሳኔ የመስጠት ጉዳይ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው በመሆኑ ሲወስኑ ሥነምግባራዊ እና ከጥቅም ግጭት የጸዱ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል። 

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም ዘርፉ ለሙስናና ብልሹ አሰራሮች ተጋላጭ በመሆኑ አመራሩ በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል። 

ተቋማት የፀረ-ሙስና ትግሉን ቅንጅት በመፍጠር መስራትና በባለቤትነት መምራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በስልጠናዊ ውይይቱ በዘርፉ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አሰራሮች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ ከተሳታፊዎችም ሀሳብ፣ ጥያቄዎችና  አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

Related Posts