+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ሙስናና ብልሹ አሰራርን ማስወገድ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና ይጫወታል – ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

*****

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሂዷል።

ስልጠናዊ ውይይቱ በሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ ተቋማት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝና አመራሮች የፀረ-ሙስና ትግሉን በባለቤትነት እንዲመሩ የሚያስችል ነው።

በስልጠናው የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ማንኛውም የመንግስት ተቋም የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት መወጣት የሚችለው ማህበረሰቡን በታማኝነትና በቅንነት ሲያገልግልና የተቋሙን ሀብት በቁጠባና በውጤታማነት ሲጠቀም ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አያይዘውም በየደረጃው የሚገኘው አመራር ራሱን ወደ ውስጥ በመመልከትና ክፍተቶቹን ፈጥኖ በማረም ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል በሙሉ ቁርጠኝነት ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የመንግስት አገልግሎት ሪፎርም በዋናነት የህዝብን እርካታ ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቅሰው፥ በአሁኑ ወቅት የትኛውም ተቋም በትላንትናው የቢሮክራሲ አስተሳሰብ ዛሬ ላይ ውጤታማ ሊሆን ስለማይችል ሙስናና ብልሹ አሰራርን ማስወገድ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአሰራር ስርዓትን ለመዘርጋትና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም፣ አሁንም በአመራሩና በፈጻሚው ላይ የሚስተዋሉ የአመለካከትና የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት የግድ እንደሚል ተናግረዋል።

ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በስራ ክፍላቸው ላሉ ኃላፊዎችና ፈጻሚዎች በማካፈል፣ ተቋሙን ከሙስና የጸዳ፣ ተገልጋይን የሚያረካና ሀብትን በቁጠባ የሚጠቀም በማድረግ የዘላቂ ማህበራዊ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፤ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ! በሚል መሪ ቃል ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተካሄደው ስልጠናዊ ውይይት የተገኙት ተሳታፊዎች ሀሳብ፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች አንስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

Related Posts