+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

በደቡብ ኮሪያ ለፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሚያዚያ 25/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከደቡብ ኮሪያ የፀረ-ሙስና እና ሲቪል መብቶች ኮሚሽን ጋር በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ዙሪያ በተፈራረሙት የጋራ ስምምነት መሰረት ለኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች የዓቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው የፀረ-ሙስና ህጎች ትግበራ፣ በተቋማት የጥቅም ግጭት መከላከል፣ በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እና የሀብት ምዝገባ መረጃ የማጣራት አፈጻጸም፣ የተቋማት ኃላፊዎች የሥነምግባር ኮድ አፈፃፀም፣ የፀረ-ሙስና ትግል ሥልጠና አሰጣጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

እንዲሁም የደቡብ ኮሪያ የፀረ-ሙስና ትግል አሰራርና ውጤታማነት ባተኮሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ በሀገራችን በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ዙሪያ ያለውን አሰራር እና ልምድ ለኮሪያ የፀረ-ሙስና እና ሲቪል መብቶች ኮሚሽን አመራሮች እና አባላት አካፍለዋል፡፡

ከደቡብ ኮሪያ የተገኘው ልምድ የሀገራችንን የፀረ-ሙስና ትግል በውጤታማነት ለመምራት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል፡፡

ከአፕሪል 27 እስከ ሜይ 2/2026 እ.ኤ.አ የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና የኮሪያ ፀረ-ሙስና እና ሲቪል መብቶች ኮሚሽን እና የኮሪያ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ( KOIKA) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts