+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ኮሚሽኑ በዘርፎች በተጠኑ የአሰራር ሥርዓት ጥናቶች ላይና በዲጂታል የሀብት ምዝገባ ዙሪያ ውይይት አካሄደ


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ) የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከዘርፍ ፎረም አመራሮችና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር በ26 ዘርፎች በተጠኑ የአሰራር ሥርዓት ጥናቶች ላይና በዲጂታል የሀብት ምዝገባ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት ዘርፍ ም/ኮሚሽንር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው ባለፋት ዘጠኝ ወራት በሙስና መከላከል ሥራ ላይ ውጤታማ ተግባራት እንደተከናወኑ ገልፀው፤ በቀጣይ ወራትም በእቅድ የተያዙ ቀሪ ተግባራት መጠናቀቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ በ26 ዘርፎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የአሰራር ሥርዓት ጥናት ሪፖርት በኮሚሽኑ የሙስና መከላከልና ጥናት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው አቅርበዋል። በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፥ በጥናቱ ላይ ጥሩ ስራዎችን የሰሩና ወደ ኋላ የቀሩ ዘርፎች ተገምግመዋል፡፡

እንዲሁም በውይይት መድረኩ በተያዘው በጀት ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በዘርፎች የተከናወነ የዲጂታል ሀብት ምዝገባ ሪፖርት በኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባና የጥቅም ግጭት መከላከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኮከብ አንበርብር አቅርበዋል።

በቀረበው ሪፖርትም እንደተመላከተው በዲጂታል ሀብት ምዝገባ ሥራ ጥሩና ደካማ አፈጻጸም ያላቸው ዘርፎችን በመለየት ለመገምገም ተችሏል።

በመድረኩም ከተሳታፊዎች ሀሳቦች፣ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በመድረኩ በተገኙ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

Related Posts