+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ(ATC) ታወር ግንባታ ግዥ የጨረታ ሂደት ላይ የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ምክረ ሀሳብ አቀረበ

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ(ATC) ታወር ግንባታ ግዥ የጨረታ ሂደት ላይ የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1236/2013 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀፅ 4 መሠረት ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሲጠረጥር ወይም ጥቆማ ሲደርሰው ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ሂደቱ እንዲቋረጥ የማድረግ ስልጣን አለው፡፡

በዚህም፣ መሠረት በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በያቤሎ በደብረማርቆስ  እና በሚዛን አማን ኤርፖርት የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ(ATC) ታወር ግንባታ ግልጽ ጨረታ ሂደት ላይ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል፡፡

በግዥ ሂደቱ፣ ለአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ (ATC) ማማዎቹ ግንባታ ግልጽ ጨረታ አየር ላይ የቆየባቸው ቀናት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጨረታ በአየር ላይ የመቆየት ጊዜን የመወሰን ኃላፊነት ያለው ቢሆንም ሰፊ ተወዳዳሪዎችን ከመሳብ አንጻር የቆይታ ጊዜው ቢሰፋ የተሻለ አማራጭ ያሰፋል የሚልና በሌሎች የክልል ከተሞች የተገነቡና በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ የታወር ግንባታዎች የጥራት ችግር አላስፈላጊ የጊዜ መጓተት መንግስትን ለተጨማሪ ወጪና የጊዜ ብክነት  የዳረጉ መሆኑ በጥናት ግኝቱ የተመላከተ ነው፡፡

በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋዉና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ ዮሃንስ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የግዥ ጨረታ ሂደቱና አፈጻጸሙ የጥናት ግኝትና  ምክረ ሀሳብ ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት የተደረገ ሲሆን፣ በቀረቡት ግኝቶችና ምክረ ሀሳቦች መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በቀጣይ በተቋሙ የሚከናወኑ የግዥ ሂደቶች ከሙስና እና ብልሹ አሠራር የጸዱ ሆነው እንዲፈጸሙ የሚያስችል ምክረ-ሐሳብ ተሰጥቷል።

በተለይ በአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ(ATC) ታወር ሥራ ላይ የሚስተዋሉ የጥራትና በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ አለመጠናቀቅ ችግሮችን አመራሩ በየጊዜው ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡ ለአብነት የአሶሳ፣  የጋምቤላና የሰመራ  ታወር ግንባታ ተጠቃሽ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

Related Posts