+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ኮሚሽኑ ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ-ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሄደ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 24/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ‘‘የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፣ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ’’ በሚል መሪ ቃል ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ-ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሄዷል።

በስልጠናዊ ውይይቱ ላይ የተገኙት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አብረሃም በላይ (ዶ/ር)፤ ዘርፋችን ሰፊ ፕሮጀክቶችን እና ሀብትን የሚያስተዳድር በመሆኑ አመራሩ ሥነምግባርን የተላበሰ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸው፤ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል አመለካከት ላይ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላቸው የስልጠናው ዋና ዓላማ በዘርፉ የሚስተዋሉ የሙስና ሥጋቶችን በመቀነስ ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭትን ማስተዳደር የሚችል አመራር ለመፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም ኮሚሽኑ ሙስናን ከመከላከል አኳያ በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ላይ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

እንደ መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ያሉ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ፕሮጀክቶች የሚተገብሩ ተቋማት የጥቅም ግጭትና ብልሹ አሰራሮች እንዳይከሰቱ በባለቤትነት መታገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በሥልጠናዊ ውይይቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ ዋና ዋና የሙስና ሥጋት እና ተጋላጭነት መገለጫ የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች፣ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts