+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ በቤተሰብ እና ማህበራዊ ተቋማት አማካኝነት ለማጎልበት በትብብር ለመሥራት የሚያስችል ምክክር ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ አመራሮች ጋር ተደርጓል

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ በቤተሰብ እና ማህበራዊ ተቋማት አማካኝነት ለማጎልበት በትብብር ለመሥራት የሚያስችል ምክክር ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ አመራሮች ጋር አድርጓል፡፡

ኮሚሽኑ አገራዊ የፀረ-ሙስና ትግል ውጤታማ እና ዘላቂ እንዲሆን በትኩረት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታ ነው።

በዚህ ወሳኝ አገራዊ አጀንዳ በርካታ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉ ቢሆንም፣ በቀጣይ በትብብር የሚመራበት የአሰራር ሥርዓት እየተዘረጋ ይገኛል።

ትውልዱን በሥነምግባር ማነጽ ከሥር መሠረቱ መሆን እንዳለበት እና ቤተሰብ እንዲሁም ቅድመ-መደበኛ እና መደበኛ የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ከተለመደው የዕውቀት እና ክህሎት ግንባታ ባሻገር የመልካም ባህሪ ግንባታ በአርዓያነት የሚፈጽሙበት ተገማች አገራዊ የአሰራር ሥርዓት ማጠናከር የትብብሩ ትኩረት ጉዳይ እንደሆነ በውይይቱ ተመላክቷል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

Related Posts