+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ውሳኔዎችን ስናሳልፍና ጉዳዮችን ስናስፈጽም ከጥቅም ግጭት የጸዱ መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል – ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 24/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ-ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሂዷል።

በስልጠናዊ ውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአጠቃላይ ትምህርትና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ስልጠናዊ ውይይቱ ከአመራሩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው መሆኑን ገልጸው፥ ውሳኔዎችን ስናሳልፍና ጉዳዮችን ስናስፈጽም ከጥቅም ግጭት የጸዱ መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

መንግስት ትውልድን መቅረጽ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ዘርፉ የትውልድ ሥነምግባር ማነጽ ላይ ለውጥ በሚያመጣ መንገድ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም በምንሰራቸው ስራዎች ላይ ግልጽ መሆንና ከጥቅም ግጭት አንጻር በምን ሁኔታ ማስኬድ እንዳለብን መረዳት ይገባናል፤ እንደነዚህ አይነት ጉዳዮችን ለመቅረፍም አሰራሮችን የማዘመንና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ይጠበቃል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽን ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላችን ስልጠናዊ ውይይቱ ሙስናን መከላከል የሚያስችል ግንዛቤ በከፍተኛ አመራሩ ለመፍጠር እና በተቋማት የመልካም ሥነምግባር ባህል እንዲዳብር ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

በተለይም በትምህርት ዘርፉ የሙስና ተጋላጭነት ሂደቶችን በተጠናከረ ቅንጅት ለመምራትና የፀረ-ሙስና ትግሉን በባለቤትነት እንዲመራ ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።

ዘርፉ ትውልድን ማነጽ ላይ የሚሰራ በመሆኑ ከእኛ ተቋም ጋር ያመሳስለዋል ያሉት ም/ኮሚሽነሩ በሥነምግባር የታነጸ ትውልድ በመገንባት ሙስናን መከላከል እንደሚገባው ገልጸዋል።

በሥልጠናዊ ውይይቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ ዋና ዋና የሙስና ሥጋት እና ተጋላጭነት መገለጫ የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ቀርበው ሰፊ ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

“የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፣ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ስልጠናዊ ውይይት የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts