+251115579202 / 0953222255 / 0953222255Kazanchiz Addis Ababa, Ethiopia

ከፍተኛ አመራሩ አርዓያ በመሆን የፀረ-ሙስና ትግሉን ከፊት ሆኖ በመምራት የራሱን ሚና ሊወጣ ይገባል –  እንደገና አበበ (ዶ/ር)


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሚያዚያ 7/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን “የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፤ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ!” በሚል መሪ ቃል በሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ስልጠናዊ ውይይት ከቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር አካሂዷል።

በስልጠናዊ ውይይቱ ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር እንደገና አበበ ከፍተኛ አመሪሩ አርዓያ በመሆንና የፀረ-ሙስና ትግሉን ከፊት ሆኖ በመምራት ከሙስና የፀዳ ሀገር እውን ለማድረግ የራሱን ሚና መጫወት አለበት ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በንግግራቸው ስልጠናዊ ውይይቱ በዘርፋችን ያሉ ክፍቶችን በመለየት የአሰራር ስርዓቶቻችንን እንድናሻሽል የሚያግዝ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የፌደራል የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው፣ አመራሩ የህዝብን ሀብት የሚያንቀሳቅስ በመሆኑ በፀረ-ሙስና ትግሉ ቁርጠኛ ሆኖ መስራት አለበት ብለዋል።

ውሳኔ አሰጣጥ የእየአንዳንዱ አመራር የዕለት ተዕለት ተግባር በመሆኑ ሲወስን ሥነምግባራዊ በሆነና ከጥቅም ግጭት የፀዳ መሆን እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የጥቅም ግጭት እያወቅንም ሆነ ሳናውቅ ሊፈጠር ይችላል ያሉት ም/ኮሚሽነሩ፣ ካጋጠመ እንዴት እናስተዳድረው የሚለውን ለመረዳት ግንዛቤ መውሰዱ ተገቢ ነው ብለዋል።

ስልጠናዊ ውይይቱም አመራሮች በዕለት ተዕለት የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመቅረፍና ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፣ ይህ አይነቱ ስልጠና ወደ ሰራተኛው ወርዶ መሰጠት እንዳለበትም አሳስበዋል።

ሥነምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት የአመራሩ ፈታኝ ሆኔታዎች በመሆናቸው እንዴት መፍታት አለብን የሚለውን መገንዘብና ማስተዳደር ይገባል ያሉት ደግሞ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሽ ግርማ ናቸው።

በስልጠናው ውይይቱ የዘርፉ የሙስና ተጋላጭ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ከተሳታፊዎች ሀሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽና ማብራርያ ተሰጥቶባቸዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts