ሙስናን ለመግታት የሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) ሚኒስትር የሾመችው አገር

ሙስናን ለመግታት የሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) ሚኒስትር የሾመችው አገር

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ ሙስናን ለመታገል በሚል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራች ሚኒስትር በካቢኔያቸው ማካተታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስሪት የሆነችው ሚኒስትር ‘ዲዬላ’ የሚል ስያሜ የተሰጣት ሲሆን በአልባንያ ‘ጸሀይ’ የሚል ትርጉም እንዳለው ተነግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱን ባህላዊ ልብስ ለብሳ የምትታየውን ሚኒስትር ባስተዋወቁበት መልዕክታቸው፥ የጉቦና የእጅ ጥምዘዛ ማስፈራሪያዎች ስጋት የለባትም ነው ያሉት፡፡

የመንግስትን ስራዎች የሚያከናውኑ ተቋማትንና ኩባንያዎችን ለመምረጥ የሚከናወኑ ጨረታዎችን ለመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣት ሲሆን፥ የመንግስትን ስራዎች ቀልጣፋ ለማድረግና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እገዛ እንደምታደርግ ታምኖባታል፡፡

ወጣቶችን ያማከለ የፀረሙስና ትግል፣ የነገ ስብዕናን ይገነባል!

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

Related Posts

Leave a Reply