Organizational Structure

1. የሥነምግባር እና የጸረ ሙስና ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈጻሚ

Activities /ተግባራት

  • በተለያዩ ርእሶች ላይ ጥራትና ተገቢነቱ የተረጋገጠ የሥልጠና ሞጁል ማዘጋጀት፣
  • ለመንግስት ተቋማትና ህዝባዊ ድርጅቶች አመራርና ሠራተኞች የፊት ለፊት የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ክህሎትና እውቀት ሥልጠና መስጠት፣
  • በዲጂታል ሥርዓት የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥልጠና መስጠት፣
  • የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥልጠና ያመጣውን የአመለካከት ለውጥ በዳሠሣ ጥናት ማረጋገጥ፣
  • በዲጂታል እና በፊት ለፊት የሚሰጡ ስልጠናዎች ጥራትና ተገቢነት ማረጋገጥ፣

2. የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና አስፈጻሚዎች ማስተባበሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ

Activities / ተግባራት

  • በመንግስት ተቋማትና ህዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዲደራጁ እንዲሁም የተጓደሉት እንዲሟሉ መከታተል፣ መደገፍ፣
  • የሥነምግበር መከታተያ ክፍሎችን የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል አቅማቸውን ማሳደግ፣
  • የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች የሚገጥማቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ መከታተልና መደገፍ፣
  • የስነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች በተቀማት ተግባራዊ መድረጉን በሱፐርቪዥን ማረጋገጥ፣

3. የፀረ-ሙስና ህዝብ ግንዛቤ ማጎልበቻ መሪ ስራ አስፈጻሚ

Activities / ተግባራት

  • ወቅታዊና ህዝብ ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል መድረኮችን በማዘጋጀት የሕብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግ፣
  • የፀረሙስና ትግል ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ ንቅናቄዎችን መፍጠር፣
  • በዲጂታል ሚዲያ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል መልእክቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ
  • በፀረሙስና ጋዜጣ መልእክቶች ለህብረተሰብ ማሠራጨት፣
  • የባለድርሻ አካላትን በጸረሙስና ትግል ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ በትስስርና በትብብር መሥራት፣

4. የሙስና መከላከል ጥናትና ክትትል መሪ ሥራ አስፈጻሚ

Activities / ተግባራት

  • በተቋማት ለሙስና እና ብልሹ ተጋላጭነት ሥጋት ያለባቸው አሰራሮች ላይ ጥናት በማካሄድ የማሻሻያ ምክረ ሀሳብ ማመንጨት፣ ለተቋማት ግንዛቤ መፍጠርና ተግባራዊ መከታተልና ማረጋገጥ፣
  • የተሰጠው የማሻሻያ ምክረ ሀሳብ ተግባራዊ ካልተደረገ መመርመርና መክሰስ ስልጠን ላለው አካል ማሳወቅና ተግባራዊነት መከታተል፣
  • የባለድርሻ አካላት በተቋማት ውስጥ የሙስና ተጋላጭነት ስጋቶች እንዳለባቸው/ በአዲት ሪፖርት የተገለጹ የሙስና ተጋላጭነት ሥጋት ማሳያዎች/ የሚላኩ  ጉዳዮችን  ማጣራት፣ የማሻሻያ ምክረ ሀሳብ ማቅረብ፣

5. የአስቸኳይ ሙስና መከላከል መሪ ስራ አስፈጻሚ

Activities / ተግባራት

  • በህዝብ ጥቆማ መነሻነት ሊፈጸም ሂደት ላይ የሚገኘው የሙስና ወንጀል ወደ የሙስና ወንጀል ድርጊት ከመለወጡ በፊት እንዲቋራጥና ወደ ትክክለኛው አሠራር እንዲለወጥ የማሻሻያ ሃሳብ ማመንጫት፣ ተቋም አመራር ግንዛቤ መፍጠር፣
  • ወደ ትክክለኛው አሰራር እንዲቀየር የተሰጣው የማሻሻያ ሀሳብ ተግባራዊ ስለመሆኑ መከታተል፣ ማረጋገጥ፣
  • የተሰጠው የማሻሻያ ሀሳብ ተግባራዊ ካልተደረገ የመመርመርና የመክሰስ ሥልጣን ላለው ማሳወቅና ተግባራዊነት መከታተል፣

6. የሀብት ምዝገባና የጥቅም ግጭት ማስወገድ መሪ ስራ አስፈጻሚ

Activities / ተግባራት

  • በአዋጅ 668/2002 እና 1236/2013 መሠረት የመንግስት ተቋማትና ሕዝባዊ ድርጅቶች አመራሮችና ሰራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ እና እንዲያሳድሱ ማድረግ፣
  • የሀብት ምዝገባ መረጃ ማስተዳደር፣
  • የተመዘገበ ሀብት መረጃ ትክክለኛነትን በማጣራት በማረጋገጥ የጥቅም ግጭት መከላከል፣ በተገኙት ልዩነቶች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መላክ፣ መከታተል፣
  • ከፍትህ አካላት የሀብት ምዝገባ መረጃ ጥያቄ በጽሁፍ ሲቀርብ ተደራሽ ማድረግ፣

7. የዲጂታል ሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ

Activities / ተግባራት

  • በዲጂል የሙስና ወንጀል ጥቆማ መቀበያ ሲስተም የሙስና ወንጀል ጥቆማዎችን መቀበል፣ መተንተንና ማበልጸግ፣
  • በኮሚሽኑ ሙስና መከላከል ሼል ጋር በተያያዘ ሙስና ስለመፈጸሙ ማሳያዎች መኖራቸው ሲረጋገጥ ጉዳዩን  ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መላክ መከታተል፣
  • የሙስና ወንጀል  ስለመፈጸሙ ማስረጃ ያላቸውን ጥቆማዎችን ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መላክ፣ የህግ ማስከበር ሥራዎች መሠራታቸውን መከታተል፣
  • የሙስና ወንጀል ያልሆኑ ጉዳዮችን  ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለሚመለከታቸው አካልት መላክ፣
  • የሙስና ወንጀል ጥቆማ መረጃዎችን መተንተን ስታስቲክስ ሪፖርት ማዘጋጀት ማቅረብ፣

8. የፀረ ሙስና ህጎችና የዓለም አቀፍ ስምምነቶች አፈጻጸም ማስተባበሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ

Activities / ተግባራት

  • የሀገሪቱ የፀረሙስና ትግል እንቅስቃሴ (ማስተመር፣ ሙስና መከላከል እና የሙስና ወንጀል ህግ ማስከበር) ውጤታማነት መገምገም፣
  • በሀገሪቱ ለተቋማት አሰራር የሚወጡ ህጎች ሙስናን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ እንዲወጡ ማማከር፣
  • ሀገሪቱ የፈረመቻቸውን የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩን መንግስታት የፀረሙስና ትግል ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ መከታተል፣ አፈጻጸሙን መገምገምና ሪፖርት ማቅረብ፣
  • የሀገሪቱን የፀረሙስና ትግል ውጤታማ ለማድረግ ከአህጉርና የዓለምአቀፍ አቻ ተቋማትና ሌሎች ድርጅቶች ትስስር መፍጠር፣ በቅንጅት መሥራት፣
  • በፀረሙስና ዙሪያ በቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፍ መድረኮች ላይ ኢትዮጵያውን ወክሎ መሳተፍ፣
  • ሀገራዊ የፀረ ሙስና ትግል የሚያግዝ ሀብት ለማመንጨት ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት መስራት፣ ሀብት ማመንጨት እና ጥቅም ላይ ማዋል፣

9. የኮሚሽነር ፅ/ቤት ኃላፊ

Activities / ተግባራት

  • በኮሚሽኑየህግ አገልግሎት መስጠት፣ ኮሚሽኑን ወክሎ በፍርድ ቤት ክርክር ማካሄድ፣ በከሚሽኑ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ማዘጋጀት ማሻሻል፣
  • በኮሚሽኑ የፋይናንስና ክዋኔ አዲት ማካሄድ፣የግኝቶች ማሻሻያ መከታተል
  • የኮሚሽኑ ሼል ኃላፊዎችና ሠራኞች የሥራ ሥነምግባር መከታተል፣የሙስና መከላከል ጥናት ማካሄድ፣ የሙስና መረጃዎችን ማመንጫት
  • የሥነምግባር እና የሙስና መከላከል መልእክቶችን ለህብረተሰብ ተደራሽ ማድረግ፣
  • የኮሚሽኑን ሪፎርም ሥራዎችና የመልካም አስተዳደር ሁኔታዎችን መከታተል፣
  • በኮሚሽኑ የሰው ሀብት ማሟላትና አቅም መገንባት፣ አስተዳደራዊ አገልግሎት መስጠት፣

10. የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

Activities / ተግባራት

  • እቃና አገልግሎት በግዥ ማሟላት፣ ክፍያ መፈፀምና የሒሣብ ሪፖርት ማዘጋጀና አዲት ማስደረግ፣
  • የኮሚሽኑን ንብረት ማስተዳደር፣ የሥራ አካባቢን ለሼል ምቹ ማድረግ፣
  • በኮሚሽኑ የኢንፎሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣
  • በኮሚሽኑ ስርዓተ ጾታ አካታችነትን ማረጋገጥ፣ ሠራተኞች ዕርካታን የሚያሣድጉ የማህበራዊ አገልግሎቶችን መስጠት፣
  • የኮሚሽኑን በጀት ማስተዳደር፣ የእቅድና በጀት ዝግጅትና አፈጻጸም መከታተል፣ መገምገም፣ ሪፖርት ማቅረብ፣