ለሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚዎችና ባለሙያዎች ተልዕኮ-ተኮር የዕቅድ እና ድርጊት መርሃግብር ኦሬንተሸን ተሰጠ
ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 7/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከዘርፍ ተቋማት ሥነምግባር እና ፀረሙስና አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
ውይይቱ በቀጣይ የሚካሄዱ የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥልጠና፣ በፀረ ሙስና ህዝብ ግንዛቤ ማጎልበቻ፣ እንዲሁም በተቋማት ሁሉም ሠራተኞች፣ ስራ ኃላፊዎችና ባለሥልጣናት የሀብት ምዝገባና እድሳት፣ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል እና የሙስና መከላከል ጥናት ስራዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ 266 የዘርፍ ተቋማት ሥነምግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚዎች፣ የሙስና መከላከል ጥናት እና የሙስና መረጃ ማመንጨት እንዲሁም የሥነምግባር ሥልጠና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!











