በፎቶ ቤት ዉስጥ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መነሻነት ባደረገው ክትትል አበበ አሰፋ እና ፍቃዱ ሳሙኤል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጁ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በክፍለ ከተማው ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጎጀም በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህጋዊ ንግድ ሽፋን የተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ስለመሆናቸው በምርመራው ሂደት ማወቅ መቻሉን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ለበለጠ መረጃ ዊብ ሰይታችን ይጎብኙ
👇👇👇
https://www.feacc.gov.et

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

Related Posts