የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በሙስና የተመዘበረ ሀብት ማስመለስና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ወርክ ሾፕ አካሄዱ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደገኛ ዕፅ እና ወንጀል መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት (UNODC) በሙስና የተመዘበረ ሀብት ማስመለስና በህገወጥ ገንዘብ ዝወውር ላይ ዎርክ ሾፕ ከኖቨምበር 10-13/2025 በኬንያ-ናይሮቢ ከተማ አካሂዷል።

በተዘጋጀው ወርክሾፕ  ላይ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሀገራት ከብሩንዲ፣ ደቡብ ሱዳንና ሶማሌ በስተቀር ሌሎች ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት (የኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ጁቡቲ፣ ሩዋንዳ እና ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ) የተገኙበት ሲሆን፤ የእኛን ሀገር ጨምሮ በሙስና የተመዘበረ ሀብት ማስመለስና በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የፋይናንስ ፎረንሲክ ምርመራ አፈጻጸም እና በዚህ ዙሪያ የዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የትብብርና ትስስር ጉዳዮችን በተመለከተ የየሀገራቱ ተሞክሮዎች ቀርበዋል፡፡

በቀጣይ ሶስት ዓመታት ውስጥ የቀጠናው ሀገራት ሊተገበሩ የሚገቡ የአፈጻጸም መለኪያዎችን ሀገራቱ በጋራ በመለየት ለከፍተኛ አመራሮች ለውሳኔ  እንዲቀርብ ያፀደቁ ሲሆን በዚህም የአፈጻጸም መለኪያዎች በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ ውይይት ተደርጎበት ሲጸድቅ፤ በቀጠናው ባሉት ሀገራት ከመከናወኑም ባሻገር በተባበሩት መንግስታት የፀረ ሙስና ትግል ስምምነት መሠረት ቀጠናው የሚገምገም ይሆናል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

Related Posts