ኮሚሽኑ ለሴት አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታኅሳስ 14/2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሥርዓተ ፆታና በማህበራዊ አካቶ ትግበራ ዙሪያ ለኮሚሽኑ ሴት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቋማት አካቶ ትግበራ ባለሙያ አቶ አንዳርጌ መልካ የተሰጠ ሲሆን፣ ዓላማውም የተለያየ ልምድና ብቃት ያላቸው ሴት አመራሮችንና ሰራተኞችን ለማፍራት እንዲሁም አብሮነትን ለማጎልበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በስልጠናው መሰረታዊ ፅንሰ ሀሳቦች በስርዓተ ፆታ፣ የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎች እንዲሁም የአካቶ ትግበራ ምንነት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናው በኮሚሽኑ በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች ላይ ተሰማርተው እያገለገሉ የሚገኙ ሴት አመራሮች የ“ይቻላል” መንፈስን በማጎልበት ያላቸውን ዓቅም ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚረዳ ተጠቁሟል፡፡

ኮሚሽኑ ያቀዳቸው ዕቅዶች እንዲሳኩ የሴቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ፣ የሴቶችን የመፈጸም ዓቅም ለማሳደግና ተጨማሪ ሴት አመራሮችን ለማፍራት የሚያግዙ መሰል ስልጠናዎች ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ተብሏል።

በስልጠናው ከተለያዩ የስራ ዘርፎች የተውጣጡ 69 ሴት አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር !

ለበለጠ መረጃ ድረ ገፁን ይጎብኙ

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#Android ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

#Apple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

Related Posts