ኮሚሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የሥድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አደረገ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ታኅሳስ 25/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የሥድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርጓል።

በሥራ አፈጻጸም ግምገማው ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ)፤ የኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ትግል ያለበትን ነባራዊ ሁኔታና መጻኢ ጉዞ መፈተሽ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

መንግሥት ለፀረ-ሙስና ትግሉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ ለትግሉ ባለቤት የሆነው ሕዝብም በንቃት መረጃ በመስጠት ረገድ እያደረገ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም መንግሥት የትውልድ ሥነምግባር ግንባታን ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራበት መሆኑንና የተቋማት መሪዎችም በየደረጃው ሙስናን በመታገል ረገድ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን የገለጹት ኮሚሽነር ሳሙኤል፤ ለስኬቱ የአመራሩና የሠራተኛው የሥራ ቅንጅትና ትብብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰዋል። በቀጣይም ይህ ትብብር ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ የተቋማዊ ለውጥ፣ የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በሪፖርቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶች ላይ ሰፊ ግምገማ የተደረገባቸው ሲሆን፣ በቀጣይ ትኩረት ተደርገው በሚሰሩ ተግባራት ላይም የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ትውልድን በሥነምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር !

ለበለጠ መረጃ ድረ ገፁን ይጎብኙ

ለሙስና ወንጀል ጥቆማ

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#Android ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

#Apple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

Related Posts