15ኛው ዙር የአገርአቀፍ የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የትስስር ጉባዔ ተካሄደ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ – ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 15ኛውን ዙር የአገርአቀፍ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የትስስር ጉባዔ አካሄደ።

ጉባዔው ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት ገምግሟል። በሪፖርቱ ከእቅዱ በላይ አፈፃፀም መመዝገቡን በግልፅ አሳይቷል።

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በሀገር ደረጃ ለ166,520 አመራሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች የሥነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ሥልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ238,615 ሥልጠና መስጠት ተችሏል፡፡በተጨማሪም በሀገር ደረጃ ለ13,354,851 የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የፀረ-ሙስና ህዝብ ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ ለ15,837,001 ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡

ለ6883 የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ7089 የአቅም ግንባታ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን የሙስና መከላከል የአሠራር ሥርዓት ጥናት ማካሄድን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 56 የሙስና መከላከል የአሠራር ሥርዓት ጥናት ለማካሄድ ታቅዶ 53 የሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ለተቋማት አስፈላጊው ምክረ- ሃሳብ ተሰጥቷል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተከናወነ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ከብክነት ማዳን ተችሏል፡፡

የሀብት ምዝገባን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 194808 አመራሮች እና ሠራተኞችን ሀብትና የገቢ ምንጭ ለመመዝገብ ታቅዶ 179549 ያህል ምዝገባ ተካሂዷል፡፡ የሙስና ጥቆማ መረጃ በተመለከተ 1847 የሙስና ጥቆማዎችን መቀበል ተችሏል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 637 የሙስና ወንጀል መረጃዎች ለሕግ አስከባሪ አካላት መተላለፋ የሂደቱን ጥንካሬ ያሳያል።

በተጨማሪም ኮሚሽኖቹ የራሳቸውን ሚዲያ በመጠቀም የሥነምግባር ግንባታና የፀረ-ሙስና ትግልን ማጠናከር እንደሚገባቸው ገልፀው፣ በተለያዩ የመረጃ መድረኮች ተደራሽነታቸውን ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ አሳስበዋል።

አመራሩ የፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ ባለቤት ሆኖ በመስራት የቅንጅት ስራውን ማጠናከር አለበት ያሉት የኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው፤ የሚዲያ አውታሮችን በአግባቡ በመጠቀም ተቋማትን የማብቃት ስራን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ትውልድን በሥነምግባር መገንባት የፀረ-ሙስና ትግል ዋነኛ መሠረት መሆኑን ጠቁመው፣ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ትውልድን ማብቃት አስፈላጊ መሆኑንም የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ አስረድተዋል።

በጉባዔው የፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ኮሚሽነሮችና ምክትሎቻቸው፣ የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች እና የስራ ኃላፊዎችን ያሳተፈ ሲሆን ጠንካራ ጎኖች የታዩባቸው እና ለቀጣይ መሻሻል ባለባቸው ሀሳቦች ላይ ውይይት ተደርጓል።

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሠራር

ለሙስና ወንጀል ጥቆማ

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#Android ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details

#Apple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

Related Posts