ችግር ፈቺ የሥነምግባር ግንባታ ሥልጠናዎች ተቋማት ሙስናን በብቃት እንዲከላከሉ የሚያስችል ነው

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 8/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሥልጠና ጥራትና ተገቢነት ላይ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በምክክር መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒኤችዲ) ችግር ፈቺ የሥነምግባር ግንባታ ሥልጠናዎች ተቋማት ሙስናን በብቃት እንዲከላከሉ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም መድረኩ እስካሁን የተሰጡ ስልጠናዎች ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ በመገምገም ለቀጣይ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠናዎች ጥራትና ተገቢነት ላይ ምክክር ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።

በዚህ ግምገማ ችግር ፈች የሆኑ ሁለት የሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተድርጎባቸዋል።

በግምገማ መድረኩ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ትውልድን በሥነምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር !

ለሙስና ወንጀል ጥቆማ

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

Related Posts