ኮሚሽኑ ከውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘርፍ-ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሄደ


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ የካቲት 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ‘‘የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት፣ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ’’ በሚል መሪ ቃል ዘርፍ-ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሂዷል።

ስልጠናዊ ውይይቱ ከፍተኛ አመራሩ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ በዘርፉ የሙስና ሥጋት እና ተጋላጭነትን በመለየት የጋራ መግባባት መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

በስልጠናዊ ውይይቱ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ መንግስት በሙስና መከላከልና የአቅም ግንባታ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለዚህም ትልቁ ድርሻ የአመራሩ ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም ካለማወቅና በአቅም ማነስ የሚመጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የሥነምግባር እና ሙስና ጉዳይ በቁርጠኝነት ከተሰራ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መቅረፍ ይቻላል ያሉት ሚኒስትሩ፤ እንደእኛ ዘርፍ ለማህበረሰቡ ሰፊ አገልግሎት የምንሰጥ በመሆኑ የመብራትና የውሃ አገልግሎት አሰጣጣችን ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ከአመራሩ ቁርጠኝነት ይጠበቃል ብለዋል።

የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በበኩላቸው ስልጠናው ለእያንዳንዳችን ወሳኝና አስፈላጊ በመሆኑ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደታችን ከሥነምግባር አኳያ እየቃኘን እንዲሁም የጥቅም ግጭትን በመከላከልና በመምራት ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የሚጸየፍ ትውልድ ማፍራት የሁላችንም ግብ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

ስልጠናው ከአመራሩ በተጨማሪ እስከታችኛው የዘርፉ መዋቅር ላሉት ሙያተኞች በአጭር ጊዜ መሰጠት እንዳለበትም አቅጣጫ ሰጥተዋል።

እንደ ሀገር ከተቀመጡ የመቀነስ ግቦች ውስጥ ሙስናን የመቀነስ ግብ አንዱ በመሆኑ የተቋማት አመራሮች ችግሩን በበላይነት መምራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ደግሞ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽን ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ ናቸው።

ግቡን ለማሳካት ተቋማት የሥነምግባርና የሙስናን ጉዳይ በእቅዶቻቸው አካተው መተግበርና አፈጻጸማቸውንም በየጊዜው መገምገም አለባቸው ያሉት፥ ም/ኮሚሽነሩ ለዚህም አሰራሮችን ማዘመንና አገልግሎቶችን ከሰው ንክኪ ነጻ ማድረግ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሥልጠናዊ ውይይቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ ዋና ዋና የሙስና ሥጋቶች እና ተጋላጭ የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች በዝርዝር መመልከት የተቻለ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና ሀሳቦች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts