የዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ስምምነት አስፈፃሚ የባለድርሻ ተቋማት አመራሮች እና የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካዮች የምክክር እና አቅም ግንባታ መድረክ ተካሄደ


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ  መጋቢት 24/2018 ዓ.ም) የዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ስምምነት አስፈፃሚ የባለድርሻ ተቋማት አመራሮች እና የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካዮች የምክክር እና አቅም ግንባታ መድረክ ተካሄዷል።

የመድረኩ ዓላማ የፀረ-ሙስና ስምምነቱ አስፈፃሚ ባለድርሻ ተቋማት በስምምነቱ መነሻ የተዘጋጀው አገራዊ የፀረ-ሙስና ትግል ማስፈጸሚያ ሕጎች፣ ስትራተጂ እና ተቋማዊ አቅም ያለበትን ሁኔታ ለመገምገም ነው።

የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን (UNCAC) በዓለምአቀፍ ደረጃ ብቸኛው የፀረ-ሙስና ሰነድ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም የዚህ ኮንቬንሽን አባል በመሆኗ የሙስና መከላከያ እርምጃዎችን በማጠናከር ዓለምአቀፍ ትብብር ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች።

የዓለምአቀፉ የፀረ-ሙስና ስምምነት አስፈፃሚ ባለድርሻ ተቋማት የሆኑት የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን (የስምምነቱ አገራዊ ተወካይ)፣ ፍትህ ሚኒስቴር (የሙስና ወንጀል ክስ የሚመራ)፣ የፌዴራል ፖሊስ(የሙስና ወንጀል ምርመራና መዝገብ ዝግጅ)፣ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት (ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መከላከል) ላይ ሚና ተሰጥቷቸዋል።

እንዲሁም ገንዘብ ሚኒስቴር ፣ ብሔራዊ ባንክ፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችና ሚዲያ ተቋማት ጨምሮ 12 ተቋማት ናቸው።

በመድረኩ አገራዊ የፀረ-ሙስና ትግል ቅንጅታዊ አሰራር ሥርዓት ከማጠናከር አንጻር፣ የባለድርሻ ተቋማት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

እንዲሁም በቆይታቸው በኮንቬንሽኑ አንቀጾች አፈፃፀም፣ መረጃ አሰባሰብ እና የሪፖርት አቀራረብ ስልቶች ላይ ጥልቅ ውይይት አካሂደዋል። በቀጣይ የፀረሙስና ስምምነቱ አባል አገሮች የአቻ ለአቻ ግምገማ ሥራዎች አስቻይ ሁኔታ የሚፈጠር ይሆናል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://iphone.apkpure.com/app/ncrs/com.codewaveet.ecis

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts