የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች በ2018 በጀት ዓመት 9 ወራት የሥራ ክፍሎች ውጤት አመልካች ተግባራት የእቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማዊ ውይይት አካሄዱ


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 29/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራርና ሠራተኞች በ2018 በጀት ዓመት ባለፋት ዘጠኝ ወራት የሥራ ክፍሎች ውጤት አመልካች ተግባራት የእቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማዊ ውይይት አካሂደዋል።

በግምገማዊ ውይይቱ በሙስና መከላከል ዘርፍ፦ የሙስና መከላከል ጥናት፣ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል እና የሀብት ምዝገባ እና ትክክለኛነት ማጣራት ሥራ ክፍሎች፤ በሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ፦ የፀረ-ሙስና የህዝብ ግንዛቤ ማጎልበቻ፣ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ስልጠና እና የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና አስፈፃሚዎች ማስተባበሪያ ሥራ ክፍሎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል።

በተጨማሪም የዲጂታል ሙስና መረጃ አስተዳደር፣ የፀረ-ሙስና ህጎችና አለምዓቀፍ ሥምምነቶች ማስተባበሪያ እና የተቋማዊ ለውጥ ሥራ ክፍሎች የ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውጤት አመላካች ተግባራት የእቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።  

ከቀረቡ ሪፖርቶች ውስጥ ለከፍተኛ አመራሩ ላይ ትኩረት በማድረግ ስልጠና መሰጠቱ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሥነምግባር አምሳደሮችን የማፍራት ሥራ መሰራቱ፣ ሀገር አቀፍ የመከታታያ ክፍሎች ትስስር መፈጠሩ፣ በዘርፎች ላይ ችግር ፈች ጥናቶች እየተከናወኑ መሆኑ፣ በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ ከአሰራር ወጪ ያሉ ሂደቶችን የማቋረጥ ምጣኔ እያደገ መምጣቱ እና የሀብት ምዝገባ ስራ በዲጂታል ሥርዓት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ በ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በጥንካሬ ተወስደዋል።

እንዲሁም የሙስና መረጃዎች በዲጂታል ሥርዓት ሳይባክኑ ዜጎች በተለያዩ አማራጮች ጥቆማ እያቀረቡ መሆኑና ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሠራቱ፤ የዓለምዓቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ሀገራዊ የትስስርና የትበብርር ሥራዎች መጠናከራቸው፤ በአጠቃላይ የተቋምን የአሰራር ሥርዓት ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸው የሚሉት በዋናነት የነበሩ ጥንካሬዎች ናቸው።

በመድረኩ በ9 ወራት የተሰሩ ስራዎች አበረታች እንደሆኑ በተሳታፊዎች የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይ በክፍተት የታዩ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ እቅዶችን ሙሉ በሙሉ መተግበር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በሪፖርቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶች ላይ ሰፊ ግምገማ የተደረገባቸው ሲሆን፣ በቀጣይ ትኩረት ተደርገው በሚሰሩ ተግባራት ላይም የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts