ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ(ፒ.ኤች.ዲ) ከኮሪያ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (KOIKA) የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄዱ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ(ፒ.ኤች.ዲ) ከኮሪያ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (KOIKA) የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ላይ ቀጣይነት ያለው ሥራ በጋራ ለመስራት ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱም በፀረ-ሙስና ህጎች ትግበራ፣ በተቋማት የጥቅም ግጭት መከላከል፣ በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፣ በሀብት ምዝገባ መረጃ የማጣራት አፈጻጸም፣ በተቋማት ኃላፊዎች የሥነምግባር ኮድ አፈፃፀም፣ በፀረ-ሙስና ትግል ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተመላክቷል።

የኮሪያ የሥነምግባር ግንባታና የፀረ-ሙስና ትግል ልምድ ለሀገራችን ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለውና ትግሉን በውጤታማነት ለመምራት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ሙስናን ለመከላከል ዲጂታል አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን፣ ይህም የሀገር ውስጥ ኢንቨስትምንትን ለመሳብ አስቻይ ሁኔታ እንደሚፈጠርና ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ እና የኮሪያ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (KOIKA) በትብብር የሚሰሩ ሲሆን፣ በዚህም ለኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች በኮሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

Related Posts