አገርዓቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የትስስር ጉባኤ ተካሄደ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም) 16ኛው አገርዓቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ የመካከለኛ ዘመን ስትራቴጂክ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ ሶስት አመታት ስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ላይ ግምገማዊ ውይይት ተካሂዷል።

አገርዓቀፍ የትስስር ጉባኤው ባለፉት ሶስት አመታት በሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና መከላከል፣ በተቋማዊ ማስፈጸም አቅም ግንባታ ጋር በተያያዘ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥና ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ ስምምነት በመፍጠር የተቀናጀ ዘርፍ ተኮር የፀረ-ሙስና ትግል በውጤታማነት ተግባራዊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

በጉባኤው የ2016-2018 በጀት ዓመት የመካከለኛ ዘመን የልማትና የኢንቨስትመንት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ ሶስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በትስስር ጉባኤው ባለፉት ሶስት ዓመታት የተከናወኑ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች፣ በአፈጻጸም የታዩ ጠካራ ጎኖችና ክፍተቶች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል፡፡

በቀጣይ ሶስት ዓመታትም በትውልድ ሥነምግባር ግንባታ፣ ሙስናን አስቀድሞ መከላከል፣ የፀረ-ሙስና ትብብር እና በተቋም ግንባታ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡

በትስስር ጉባኤው የፌደራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ም/ኮሚሽነሮች እና የኮሚሽኑ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

NCRS ሞባይል መተግበሪያ

ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details…

ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts