ለኮሚሽኑ ሴት አመራርና ሠራተኞች “የሴቶች ሚና በሥነምግባር ግንባታ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም) ለፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሴት አመራርና ሠራተኞች “የሴቶች ሚና በሥነምግባር ግንባታ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት በኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ ትውልድን በመልካም ሥነምግባር በማነጽ በኩል የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ ትውልድን በማስቀጠልና ሀገርን ወደ ብልፅግና ለማድረስም ድርሻቸው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም ትውልድን በሥነምግባር ለመገንባትና ሙስናን ለመከላከል ቤተሰብ፣ የኃይማኖት ተቋማት እና የባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። ለዚህም በተሰማራንበት የሥራ መስክ በሥነምግባራችን አርዓያ በመሆን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ልንከላከል ይገባል ብለዋል።

በኮሚሽኑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መንበረ እሸቱ በበኩላቸው፥ ሴቶች ለትውልድ ሥነምግባር ግንባታ መሠረት ናቸው ብለዋል።

አክለውም ሙስና ሕጻናትን፣ ቤተሰብን፣ የትምህርትንና የጤና ተቋማትን የሚጎዳ መሆኑን ገልፀው፥ ችግሩን ለመከላከልም የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ስልጠናው በአገርዓቀፍ የፀረ-ሙስና ምርምር ትስስር አባል ተሰፋዬ ሂርጳሳ (ዶ/ር) የተሰጠ ሲሆን፥ ከሰልጣኞች ጥያቄ፣ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።