የሥልጠና ጥራትና ተገቢነት ኮንፈረንስ ተካሄደ



(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከዘርፍ ፎረም አመራሮችና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር የሥልጠና ጥራትና ተገቢነት ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡

ኮንፈረንሱ ባለትፉት 9 ወራት የተሰጡ ስልጠናዎች ምን ያህል ጥራትና ተገቢነታቸውን የጠበቁ ናቸው የሚለውን ለመገምገምና በቀጣይ የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ ለማስቀጥ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ ባለፉት ወራት ሲሰጡ የነበሩ ስልጠናዎች ዘርፍ ተኮር በመሆናቸው ውጤታማና ችግር ፈች እየሆኑ መምጣታቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚዎች በተቀናጀ የሙስና መከላከያ ስልቶች ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

በመድረኩ በ26 ዘርፎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የአሰራር ስርዓት ጥናት ሪፖርት ቀረቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን፥ በጥናቱ ላይ ጥሩ ስራዎችን የሰሩና ወደ ኋላ የቀሩ ዘርፎች ተገምግመዋል፡፡

እንዲሁም በተያዘው በጀት ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በዘርፎች የተከናወነ የዲጂታል የሀብት ምዝገባ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በመድረኩም ከተሳታፊዎች ሀሳቦች፣ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Related Posts