17ኛው አገርዓቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ ተካሄደ

17ኛው አገርዓቀፍ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ ግምገማዊ ውይይት ተካሂዷል።

አገርዓቀፍ የትስስር ጉባኤው በ2018 በጀት አመት በሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና ቅድመ-መከላከል፣ በተቋማዊ ማስፈጸም አቅም ግንባታ ጋር በተያያዘ ለፀረ-ሙስና ትግሉ አጋዥና ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ ስምምነት በመፍጠር የተቀናጀ ዘርፍ ተኮር የፀረ-ሙስና ትግል በውጤታማነት ተግባራዊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ ተመላክቷል፡፡

በጉባኤው የአገር ዓቀፍ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በትስስር ጉባኤው በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል እና በተቋማዊ ማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች በአፈጻጸም የታዩ ጠካራ ጎኖችና ክፍተቶች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል፡፡

በ2019 በጀት ዓመትም በትውልድ ሥነምግባር ግንባታና ሙስናን አስቀድሞ መከላከል ፕሮግራም፣ የፀረ-ሙስና ትግል ተቋማዊ ቅንጅት፣ ትብብርና ትስስር ማጎልበት ፕሮግራም እንዲሁም በተቋም ግንባታ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡

በትስስር ጉባኤው የፌደራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ም/ኮሚሽነሮች እና የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

Related Posts