አገርዓቀፍ የሥነምግባር ግንባታ ሥልጠና እና የሙስና መከላከል ጥናት የፋይዳ ግምገማ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ።


(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 8/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አገርዓቀፍ የሥነምግባር ግንባታ ሥልጠና እና የሙስና መከላከል ጥናት የፋይዳ ግምገማ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በምክክር መድረኩ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቴ አለነ የሙስና መከላከል ስራን ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረውን የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ የሙስና ትግሉን የሚመሩ ሰዎች በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል።

የሙስና መከላከል የመጀመሪያው ግንዛቤ መፍጠር ነው ያሉት አቶ እውነቴ አለነ በአሰራርና በአደረጃጀት የሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ውጤታማ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ፒ.ኤች.ዲ) በበኩላቸው ባለፈው የመካከለኛው ስትራቴጂክ ዘመን ችግር ፈች የሆኑ ዘርፍ ተኮር ስልጠናዎች ተሰጠዋል።

በእነዚህ ስልጠናዎች የተቋማት አመራርና ሰራተኞችን ክህሎትና አመለካከትን በመገንባት የመንግስት በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል አስቻይ ሁኔታ ፈጥረናል ብለዋል።

እንዲሁም በሁሉም ዘርፎች ዘርፍ ተኮር የሆኑ የሙስና ስጋት ጥናቶች ተደርገዋል ያሉት ኮሚሽነሩ ጥናቶች የአልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መነሻ ያደረጉ እንደሆኑም ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ በንግግራቸው የፀረ-ሙስና ትግልን ተግባራዊ ለማድረግ በተቋማት ግልጽነትና ተጠያቂነትን መፍጠር እንደሚገባ ገልጸው፣ ተቋማት ትግሉን በባለቤትነት መምራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በሙስና መከላከል ስራ አመራሩ ባለቤትና ተጠያቂነትን መርህ ማድረግ ይገባል ያሉት ደግሞ በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው ናቸው።

በሥነግባር የታነጸና ሙስናን የሚጸየፍ ዜጋ ለማፍራት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት እና ስራዎች ውጤታማ የሚሆኑት የተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች አርዓያ ሆነው ሲገኙ እንደሆነ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ ገልጸዋል።

በመድረኩ በመካከለኛው ዘመን የተከናወኑ የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ስራዎች የነበሩ ጥንካሬዎችንና የታዩ ጉድለቶችን በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ለማመላከት ተችሏል።

በምክክር መድረኩ በመካከለኛው ዘመን እቅድ የተከናወኑ ሀገርዓቀፍ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች የሚያሳይ ሰነድ ቀርቦ ምክክር የተደረገ ሲሆን፥ ከተሳታፊዎች ሀሳብ፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

#NCRS ሞባይል መተግበሪያ

#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details…

#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

Related Posts